ለኢትዮጵያውያን ነርሶች በአቡዳቢ የሥራ ዕድል እየተመቻቸላቸው ነው

የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) ከሪስፖንስ ፕላስ ሆልዲንግ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማጆር ቶም ኩዊስ ጋር
የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) ከሪስፖንስ ፕላስ ሆልዲንግ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማጆር ቶም ኩዊስ ጋር 
  • 15 ቢሊዮን ብር ወጪ ሆስፒታል ለማቋቋም ታስቧል

ተመራቂ የጤና ባለሙያዎች ከሥራ ፈላጊነት ወደ ሥራ ፈጣሪነት እየተቀየሩ ራሳቸውንና ኅብረተሰቡን የማገልገል ሥራ እንደተያያዙት እየተስተዋለ ነው፡፡ በዚህ መልኩ እየተካሄደ ባለው እንቅስቃሴም የቤት ውስጥ ሕክምና (ሆም ሔልዝ ኬር) የማቋቋም ጅማሮና በውጭ አገር የሥራ ዕድል ለማግኘት የሚያስችሉ ሁኔታዎችን የማመቻቸቱም ተግባር በተደራጀ መልኩ ብቅ ብቅ እያለ ነው፡፡ በመካከለኛው ምሥራቅ ለነርሶች እየተካሄደ ያለውም የሥራ ዕድል ፍለጋ ይህን ሁኔታ እንደማሳያ ሊወሰድ ይችላል፡፡

መሰንበቻውን በተባበሩት ዓረብ ኤሚሬትስ ለኢትዮጵያውያን የጤና ባለሙያዎች የሥራ ዕድል ለማመቻቸት በጤና ሚኒስቴር፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽንና መቀመጫውን አቡዳቢ ባደረገው ከፍተኛ የጤና ተቋም (ሪስፖንስ ፕላስ ሆልዲንግስ) መካከል የሦስትዮሽ የመግባቢያ ስምምነት ተደርጓል፡፡

የፊርማ ሥነ ሥርዓቱ የተደረገውም ከሁለት ሳምንት በፊት የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) አቡዳቢን በጎበኙበት ጊዜ ነው፡፡

የሪስፖንስ ፕላስ ሆልዲንግ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማጆር ቶም ኩዊስ በበኩላቸው፣ ለጤና ባለሙያዎቹ የሥራ ዕድል ማመቻቸት ከጤና ሚኒስቴርና ከሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ጋር በጋራ ከምንሠራቸው ሥራዎች መካከል አንዱ ነው፤›› ካሉ በኋላ የጤና ሚኒስቴር የጤና ዘርፉን ለማሻሻል፣ የድንገተኛ አገልግሎትን ለማጠናከር የሰው ኃይል ልማትን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማከናወን ድጋፉን እንደሚሰጥና ለዚህም ቢሮውን በኢትዮጵያ ለማቋቋም በሒደት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

Dr. Dagimawi Tesfaye

ዳግማዊ ተስፋዬ (ዶ/ር) በተባበሩት ዓረብ ኢምሬትስ ሪስፖንስ ፐልስ ሆልዲንግስ (ፒጄኤስሲ) የተባለ ግዙፍ የሕክምና ድርጅት የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ናቸው፡፡ እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ፣ ድርጅቱ 25 የጤና ተቋማት ውስጥ ከ200 በላይ ኢትዮጵያውያን ነርሶች የሥራ ዕድል እያመቻቸላቸው ነው፡፡

ለመጀመርያ ጊዜ የዕድሉ ተጠቃሚ የሚሆኑት እነዚሁ ነርሶች የመጀመርያ ዲግሪ ሊኖራቸውና የሲኦሲ ፈተናም ማለፍ እንደሚጠበቅባቸው ነው ካንትሪ ዳይሬክተሩ የተናገሩት፡፡

 

Dr. Dagi Medical Consultancy

 

ይህንንም አሟልተው ለሚገኙ ነርሶች የሥራ ዕድል ወደተገኘባቸው የጤና ተቋማት ከመንቀሳቀሳቸው በፊት ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ሥልጠና እንደሚሰጣቸው፣ ሥልጠናውንም የሚሰጡት በዋናነት የደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ የጤና ባለሙያዎች ሲሆኑ የኢትዮጵያ ባለሙያዎችም እንደሚሳተፉበት ዳግማዊ ተስፋዬ ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

ከሚያስፈልጉትም ነርሶች መካከል እስካሁን የ50 የስም ዝርዝር ለፒጄኤስሲ ኢትዮጵያ መላኩን ዳይሬክተሩ አውስተዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ አዲስ አበባ ውስጥ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና እጅግ ዘመናዊ የሆነ ሆስፒታል በ15 ቢሊዮን ብር ለማቋቋም መታሰቡንም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡ እንደ ዶ/ር ዳግማዊ ማብራሪያ ይቋቋማል ተብሎ የሚታሰበው ይህ ሆስፒታል፣ የኩላሊት ንቅለ ተከላን ጨምሮ ሁሉንም ዓይነት የንቅለ ተከላ እንዲሁም የካንሰር፣ የነርቭና የጭንቅላት ሕክምና የሚሰጥበት ነው፡፡

የሆስፒታሉ መቋቋም ለሜዲካል ቱሪዝም መበልፀግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ያወሱት ዳይሬክተሩ፣ ከዚህም ባሻገር ከፍተኛ ገንዘብ እየከፈሉ ለሕክምና ወደ ተለያዩ አገሮች የሚሄዱት ሕሙማን ሕክምናውን እዚሁ እንዲያገኙና ከአቅም በላይ ከሆነ ወጪ እንዲድኑ በማድረግም የበኩሉን ዕገዛ እንደሚያበረክት አመልክቷል፡፡

Dr. Dagi Medical Consultancy